ከክብረመንግሥት የታሪክ ማሕደር – ዜድ ኃይሉ

ከክብረመንግሥት የታሪክ ማሕደር – ዜድ ኃይሉ

በክብረመንግሥት የመጀመሪያው ዘመናዊ ፎቶ ቤት ባለቤት አቶ ቶሩ ሻመና ይባላሉ
የሱቃቸውም መጠሪያ ፎቶ ቶሩ ይባል ነበር ዘመናዊ የተባለበትም ምክንያት ከዚያ በፊት ፎቶ ለመነሳት ፎቶ መሄድ ግድ ሲሆን ፎቶውም ለመታጠብ ወደሌላ ቦታ መላክ ነበረበት

ይህንን በማስቀተር ቀዳሚው ቶሩ ሻመና ናቸው፡፡ በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ ካሜራቸውን ይዘውም ይገኛሉ ፎቶም በሶስተኛው ቀን ለባለቤቱ ማስረከብ ተችሎ ነበር፡፡

ቦታውም አሁን ከባላምበራስ ዓለማየሁ በንቲ ሆቴል አጠገብ ያለው ንብረትነቱ የነከድሮ ሙሳ ቤተሰብ የነበረ እና በኍላ ጋሽ ርዕሶም ለደርቤ የሰጠውና ደርቤም ከወያኔ መግባት ጋር ደርግ የወረሰው ንብረት ለባለቤቶቹ ይመለስ ሲባል ከመጨረሻዋ ልጅ ከሲቲና ጋር ተደራድሮ ገዝቶ የራሱ እድርጎታል
የ ደርቤ ፈቅይደሩ ቡናቤት ማለት ነው::


በክብረመንግሥት የመጀመሪያው ዘመናዊ ሱቅ ባለቤት አቶ ሃብቴ ገብረየሱስ ናቸው የነ ተከስተ ሃብቴ ሱቅ ማለት ነው፡፡
ያኔ መኳንንቶቹ ውስኪ የሚራጩበት ቤት እንደነበረ ከወላጆቼ በሚገባ ተረድቻለሁ
እንግዲህ ክብረመንግሥት ጣፋጭ የክሬም ብስኩቶች ፡ ቼኮለት፤ ከረሜላ፡ ሜንታ፡ሴኮ እና ሪስ የእጅ ሰአት፡ ውስኪና የታወቁ ኮኛኮችንም ያስመጡ ነበር


በክብረመንግሥት የመጀመሪያው ሻይ ቤት ባለቤት የነበሩት አቶ ጃማ የሚባሉ የሶማሌ ተወላጅ ሶማሌያዊ ሲሆኑ ከሳቸው ጋር 12 ለሚሆኑ ሶማሌዎሽ ዬትዮጵያዊ ዜግነት መብት እንዲያገኙ ትልቁን እገዛ ያደረጉላቸው ወላጅ አባቴ አቶ ኃይሉ ሸምቡ መሆናቸውን ቆይቶም ቢሆን ከአባቴ የግል ዶኩሜንቶች ለመረዳት ችያለሁ ፡፡ሌላኛዋ ሶማሊያዊት እና የዳቦ መጋገሪያ ባለቤት የነበሩት ወ /ሮ ….. ስማቸውን ዘነጋሁ ልጃቸው ስሙኔ ስለምትባል ሃዳ ስሙኔ በመባል ይታወቃሉ ወንዱ ልጃቸው አብዶ ኮቤ ጫማ በመስራት በደንብ ይታወቃል..ቤታቸውም ከአቶ ተስፋዬ ብራቱ ቤት ወረድ ብሎ ባለ ሁለት በር የበረንዳ ቤት ነው፡፡ ሌሎቹ አብዛኞቹ ኑሯቸው ወደ በንቆ እና ኮባሶርሳ በሚወስደው መንገድ ከከተማ ወጣ ብለው ይኖሩ ስለነበር ብዙም አይታወቁም፡፡
በክብረመንግሥት መጀመሪያው ዘመናዊ ጽጉር አስተካካይ አቶ ዘለቀ ጩፋ ይባላሉ


ቦታውም አሁን የንግድ ባንክ የተሰራበት 50 ሜትር አለፍ ብሎሲሆን ከዚያ የወይዘሮ አዳነች ሲማ ቡና ቤት ነበር ፤፤
አቶ ዘለቀን ዘመናዊ ያሰኛቸው የሚጠቀሙበት ቶንዶስ እና ተሽከርካሪ ወንበር ስለነበራቸው ነው መኖሪያቸው ከ እማማ ጦቢያው በያን ቤት ጥቂት አለፍ ብሎ ከጋሽ አህመድ መሃመድ ሠዒድ ቤት ፊት ለፊት ማዶ ዳገቱ ላይ ነ ነበር፤፤


በክብረመንግሥት የመጀመሪያው ትምህርት ቤት ኩሚና ትምህርት ቤት ይባላል አሁንም በስራ ላይ ያለ ይመስለኛል
እንግዲህ ሌሎችንም ታሪኮች በምችለው መጠን አፈላልጌ ለማቅረብ እሞክራለሁ

Zed Hailu

Related Post

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *